Sunday, May 18, 2014

ይድረስ ለጥላሁን በቀለ



                                         ይድረስ ለጥላሁን በቀለ
                  እንደአንድ መርማሪ ጋዜጠኛ ዘገባህ ጥሩ እና ሌሎችንም ሊያበረታታ የሚችል ነው፡፡ ሆኖምግን ባንተ የተሰራው ስራ በአ ኤርሚያስ ድርጅት ላይ ብቻ ያጠነጠነ ነው፡፡ በመጀመሪያ ደረጃ ያንተአላማ አርሜተራ የተባለውን ድርጅት በሰራው ማስታወቂያ ላይ ራሱን ለምን የውሃዎች ንጉስ ብሎ ጠራ ይህንንም ከማስታወቂያ አነጻር ለመመርመር ነበር፡፡ ቢሆንም ይህንን ተከትሎ የመጣው ድርጅቱ ንጽህናው ባልተጠበቀ ስፍራላይ እንደሚሰራ አብረህ አየህ፡፡ ከደረጃዎች ባለስልጣን በመቀጠል እውቅና ሰጥቶናል ወዳሉት ፓስተር ነበር የሄድከወ ያነጋገርካቸው ዶክተር ሓይሉ እንዳሉት  በዛ ቦታላይ ይህ ስራ መሰራቱ ስህተትመሆኑን ነግረውሃል፡፡ በምንስ ምክንያት ነው ይህንን ሊያውቁይ የቻሉት ምክንያቱም እንደተናገርከው ፓስተር  የመመርመር ስልጣን እንደሌለው ነው፡፡ እንደእኔ ሃሳብ ይሄም አጠያያቂ ነወ፡፡
ከዚህም ሌላ የብሄረ ፅጌ ጤና ጣቢያን እንዳነጋገርክ እና እነሱም  ለአዲሰ አበባ ጤና ቢሮ እንዳመለከቱ ነግረውህ እንደነበረ ተናግረሃል ታዲያ ለምን ጤና ቢሮው ዝም አለ? አንተም ይህንን ማጣራት አልነበረብህም ወ አንተም ይህንን ማጣራት አልነበረብህም ወይ? ግን አንተ ያደረከው አርሜታን ብቻ ማጋለጥ ነበር፡፡ በተጨማሪም አቶ ኤርሚያስን ስታነጋግር የራሱን ጨምሮ ሁለት ውሃዎችን እንዳስመረመረ ሲገልፅልህ ነገሩን በማዞር የሌላ ድርጅትን ምርት ማስመርመር ወንጀል እንደሆነ ተናገርክ ሆኖም ግን የኮነንከው አርሜታን ብቻ ነበር ግን መርማሪው ለምን አልተጠየቀም? ይህ የሚያሳየው ያንተ ኢላማ አርሜታ ብቻ ነበር ይህ ደግሞ የምትሰራው ለህዝብ ሳይሆን ለራስህ ነበር ማለት ነው፡፡
                   እንደማስታወቂያም ቢሆን በእኔ አመለካከት የውሃዎች ንጉስ ማለቱ ችግር አለው ብዬ አላስብም ምክንያቱንም እንደዚህ ያለው የመጀመሪያው ድርጅት ስለሆነ ሊሆን ይችላል  ለምሳሌም  ቅዱስ ጊዮርጊስ ቢራ እራሱን የቢራዎች አውራ ብሎ እየጠራ ይገኛል  እንደዚህ የሚልበት ምክንያት የመጀመሪያው ቢራ ስለሆነ ነው፡፡ ለማጠቃለልም በእኔ እይታ  ያንተ ዘገባ በግል ፀብ ወይም እነሱ እንዳሉት ገንዘብ ጠይቀህ አልሰጥም ስለተባልክ ሊሆን ይችላል ባይ ነኝ፡፡

Friday, May 16, 2014

የ ኢትዮጵያ ሬዲዮ እና ቴሌቪዥን ድርጅት እና አጋሮቹ በአሁኑ ሰአት ከሚያራምዱት የልማታዊ ጋዜጠኝነት ጋር በተያያዘ ይመስለኛልልማታዊ የሆኑ ማሰታወቂያዎች በአሁኑ ሰአት ስፍር ቁጥር የላቸውም᎓᎓ እነዚህ ማሰታወቂያዎች ታዲያ በተመሳሳይ ሰዎች የሚሰሩና ይዘታቸውም የወረደ ተመልካችን ሊስቡ የማይችሉ ፈጠራ አልባ ናቸው᎓᎓ አብዛኛዎቹ ማለት ይቻላል የሚሰሩት በ ኢቴቪ የማስታወቂያ ጭፍሮች ሰራዊት እና ሰራዊቶቹ ነው᎓᎓ በሚገርም ሁኔታ ማስታወቂያዎቹ የስምና የ አድራሻ ለውጥካልሆነ በቀር ምንም ልዩነት አይታይባቸዉም᎓᎓ ለማሳያም ያህል ሰራዊት እና ሙሉአለም ወላይታን እናልማ የሚል ማስታወቂያ ሰሩ እንበል በመጀመሪያ የወላይታ ሙዚቃ ይከፈታል ሁለቱ ይጨፍራሉ ከዛ እየተቀባበሉ መልእክትያስተላልፋሉ በመሃል ላይ ወላይቲኛ ጣል ያደርጋሉ ከዛ እየጨፈሩ ይጨርሳሉ᎓᎓ የሚገርመው ይህ አይደለም ሌላ የጐጃም፣ጉራጌ፣ሲዳማ፣አዳማ ወዘተ የልማት ማስታወቂያ ሲኖር የሚሰሩት ሁለቱ (ሰራዊት እና ሰራዊቶቹ) ሲሆኑ ምንም አይነት ለውጥ ሳያሳዩ ለወላይታ የሰሩትን ለቀጣዮቹ ይደግሙላቸዋል እንደውም ሊያልቅ ሲል "ኑ ወላይታን በጋራ እናልማ" ብለው ከነበረ ለቀጣዮቹ የየሃገሩን ስም እየጠሩ እናልማ እያሉ ያደርቁናል᎓᎓ቢያንስ ቢያንስ እንደማስታወቂያ ባለሙያ ምናለ የሚናገሩት መፈክር እንኳን ቢቀይሩ᎓᎓ ለዚህ ችግር መንስኤ ነው ብዬ የማስበው በመሰኩ የተማረ ሰው እና ተወዳዳሪ የማስታወቂያ ድርጅቶች አለመኖር ነው᎓᎓ በእኔ ግምት ከ 80% በላይ የሚሆኑ ልማታዊ ማስታወቂያዎች የሚሰሩት በሰራዊት እና ሙሉአለም ነው᎓᎓ ግን ሌሎች የማስታወቂያ ድርጅቶች ይህንን እድል ለምን አላገኙምየሚለው ዋነኛው ጥያቄዬ ነው᎓᎓ በአሁኑ ሰዐት የፈጠራ ድርቅ ያጠቃቸው እነዚህ ማስታወቂያዎች መቼ ይሆን የተማረ ዝናብ የሚዘንብላቸውእኛስ ተመርቀን ስንወጣ ከሰራዊት እና ሰራዊቶቹ ነጥረን እንወጣ ይሆን