Friday, May 16, 2014

የ ኢትዮጵያ ሬዲዮ እና ቴሌቪዥን ድርጅት እና አጋሮቹ በአሁኑ ሰአት ከሚያራምዱት የልማታዊ ጋዜጠኝነት ጋር በተያያዘ ይመስለኛልልማታዊ የሆኑ ማሰታወቂያዎች በአሁኑ ሰአት ስፍር ቁጥር የላቸውም᎓᎓ እነዚህ ማሰታወቂያዎች ታዲያ በተመሳሳይ ሰዎች የሚሰሩና ይዘታቸውም የወረደ ተመልካችን ሊስቡ የማይችሉ ፈጠራ አልባ ናቸው᎓᎓ አብዛኛዎቹ ማለት ይቻላል የሚሰሩት በ ኢቴቪ የማስታወቂያ ጭፍሮች ሰራዊት እና ሰራዊቶቹ ነው᎓᎓ በሚገርም ሁኔታ ማስታወቂያዎቹ የስምና የ አድራሻ ለውጥካልሆነ በቀር ምንም ልዩነት አይታይባቸዉም᎓᎓ ለማሳያም ያህል ሰራዊት እና ሙሉአለም ወላይታን እናልማ የሚል ማስታወቂያ ሰሩ እንበል በመጀመሪያ የወላይታ ሙዚቃ ይከፈታል ሁለቱ ይጨፍራሉ ከዛ እየተቀባበሉ መልእክትያስተላልፋሉ በመሃል ላይ ወላይቲኛ ጣል ያደርጋሉ ከዛ እየጨፈሩ ይጨርሳሉ᎓᎓ የሚገርመው ይህ አይደለም ሌላ የጐጃም፣ጉራጌ፣ሲዳማ፣አዳማ ወዘተ የልማት ማስታወቂያ ሲኖር የሚሰሩት ሁለቱ (ሰራዊት እና ሰራዊቶቹ) ሲሆኑ ምንም አይነት ለውጥ ሳያሳዩ ለወላይታ የሰሩትን ለቀጣዮቹ ይደግሙላቸዋል እንደውም ሊያልቅ ሲል "ኑ ወላይታን በጋራ እናልማ" ብለው ከነበረ ለቀጣዮቹ የየሃገሩን ስም እየጠሩ እናልማ እያሉ ያደርቁናል᎓᎓ቢያንስ ቢያንስ እንደማስታወቂያ ባለሙያ ምናለ የሚናገሩት መፈክር እንኳን ቢቀይሩ᎓᎓ ለዚህ ችግር መንስኤ ነው ብዬ የማስበው በመሰኩ የተማረ ሰው እና ተወዳዳሪ የማስታወቂያ ድርጅቶች አለመኖር ነው᎓᎓ በእኔ ግምት ከ 80% በላይ የሚሆኑ ልማታዊ ማስታወቂያዎች የሚሰሩት በሰራዊት እና ሙሉአለም ነው᎓᎓ ግን ሌሎች የማስታወቂያ ድርጅቶች ይህንን እድል ለምን አላገኙምየሚለው ዋነኛው ጥያቄዬ ነው᎓᎓ በአሁኑ ሰዐት የፈጠራ ድርቅ ያጠቃቸው እነዚህ ማስታወቂያዎች መቼ ይሆን የተማረ ዝናብ የሚዘንብላቸውእኛስ ተመርቀን ስንወጣ ከሰራዊት እና ሰራዊቶቹ ነጥረን እንወጣ ይሆን

No comments:

Post a Comment