Friday, June 13, 2014

AXE



  AXE
   በአሁኑ ሰአት በአለማችን ቁሳዊነት የሀብት መለኪያ፣የእድገትማሳያ፣ እንዲሁም የስልጣኔ መገለጫ ሆኗል። የአንድን ሰው የኑሮ ደረጃ ለመለካት የሚያሽከረክረውመኪና፣የሚለበሳቸው ልብሶቸ፣የሚኖርበት ቤት፣እንደመስፈርት ይታያሉ። ታዲያ ይህንን መስፈርት ያሟላሰው ሃበታም፣ ተወዳጅ፣ ታዋቂ፣ወዘተ እየተባለ ይጠራል።
     የዕቃዎች ማስታወቂያ በአሁኑ ሰአት ለየት ያለ እና ቁሳዊነት የደላበት ሆኖ እየተሰራ ይገኛል። የአክሰ ዲዮዶራንት ማስታወቂያ ለዚህ አይነት ማስታወቂያ እንደማሳያ ይሆናል። ማስታወቂያው እንደሚያሳየው አንድ ሰው  አክስ ዲዮዶራንትን ሲጠቀም ሴቶች እንደሚቀርቡት ተደርጎ የተሰራ ማስታወቂያ  ነው። ይህ ማስታወቂያ ዘመኑን በትክክል መግለፅ የሚችል ጥሩ ፈጠራ የታየበት ማስታወቂያ ነው።
     ቁሳዊነት በሰፈነበት በአሁኑ ሰአት አንድን ሰወ አክስን ብትጠቀም ሴቶች ይቀርቡሃል ቢባል ግነት አይሆንም። ከላይ ለመጥቀስ እንደሞከርኩት ሰዎች የሚመዘኑት ባላቸው ነገር ስለሆነ ነው።አክስ ደግሞ አራሱን የምርጦች ምርጫ፣ ተወዳጅነትን የሚያስገኝ አድርጎ ከመመልከተ የመነጨ ነው። አክስ ይህንን ማሰታወቂያ መስራቱ በብዙዎች  ዘንድ ሴትን የበታች አድርጎ ከማየት የመነጨ ተደርጎ የታሰባል።
      ሴቶች ብቻ ሳይሆን ወንዶችም ቢሆኑ ጥሩ ልብስ የለበሰች ወይም ሆነ ሎሽን ተቀብታ ሰውነቷ ያማረች ሴትን ሲከተሉ የሚያሳዩ ማስታወቂያዎች ተሰርተዋል። ይህም ማለተ በነሱ አመለካከተ ይህ ማስታወቂያ ወንዶችን ዝቅ አድርጎ ይመለከታለ ማለት ነው።ነገር ግን ማንም ሰው ቢሆን መልካም የሆነ ነገርነ ይወዳል ስለዚህ አክስ የተቀባን ሰው  ሴቶች ቢቀርቡት ምንም ሊገርም የሚችል ነገር አይደለም።
      አክስ የሰራው ማስታወቂያ ከፈጠራ አንፃር ለየት ያለ አየነት ሲሆን ለማስተዋወቅ የተጠቀመበትም መንገድ በጣም ጥሩ የሚባል አይነት ነው። ማስታወቂያ የሚሰራው አስተዋዋቂ ድርጀቱ የኔን ምርት የጠቀማሉ ብሎ ለሚያስባቸው ተመልካቾች ሲሆን የማስታወቂያውም ይዘት የተመልካቹን ፍላጎት መሰረት ያደረገ ነው። በዚህም በኩል ስናይየአክስ ዲዮራንት ተጠቃሚ ይሆናሉ ተብሎ የሚታሰቡት በሃገራችን አነፃር ወጣቶች በተለይም የከተማ ሰዎች ናቸው። እነዚህም ሊያስደስታቸው እነዲሁም ትኩረት ሰጥተው ሊታተሉት የሚችሉት ማስታወቂያ ልክ እንደ አክሰ አይነት ያልተንዛዛ ትኩረት የሚስብ አይነት ማሰታወቂያ ነው።
      በአሁ ሰአት የሰዎች በአጭር የመግባባት ልምድ እየሰፋ ምጥቷል ( በተለይም በማስታወቂያ)። የአክስ ደንበኞች አክስ የሰራው ማስታወቂያ በአጭሩ ሊረዱት ይችላሉ። በእርሻለሚተዳደር ማህበረሰብ የሚሰራ ማሰታወቂያ ለምሳሌ የማሰዳበሪያ ማስታወቂያ ማብራራት፣ገለፃ ወዘተ ሊያስፈልገው ይችላል ምክንያቱም ይህንንማስታወቂያ የሰራንለት ማህበረሰብ ያለው የመረዳት ወይም የመገንዘብ አቅምን ያማከለ መሆን ስላለበት ነው ነገርግን አክስን ይጠቀማሉ ብለን የምናስባቸው ሰዎች ማብራሪያ ወይም ገለፃ ያለው ማስታወቂያ ብንሰራ ሊሰለቻቸው እንዲሁም ላይመለከቱት ጭምር ይችላሉ ምክንያቱም የምናብራራው ነገር እነሱ ስለሚያውቁት ነው።   
      አበዛኛዎቹ የሃገራችን ማስታወቂያዎች ከአላማ አንፃር ግባቸውን ይበታሉ የሚል ግምት የለኝም። ምክንያቱም ብዙውነ ጊዜ ማስታወቂያዎቹ የሚሰሩት ድራማዊ በሆነ መንገድ ነው ይህ ደግሞ አላማውን ከማሳካት አንፃር አቅሙ አነስተኛ ነው። ምክንያቱም ተመልካቹ ሊመለከት የሚችለው ድራማዊ የሆነውን ነገር ሲሆን መልዕከተን የመስማት አቅሙ ማለትም የዕቃውን አይነት፣አድራሻ ወዘተ ማስታወስ የሚችለው  በጣም አነስተኛ በሆነ መልኩ ብቻ  ነው።
     በአጠቃላይ  አክሰ የሰራው ማስታወቂያ እጅግ ቤጣም ጥሩ እና ለሌሎችም ምሳሌ ሊሆን የሚችል እና ተጠቃሚውንም መሰረት ያደረገ በዘፈቀደ የተሰራ እንዳልሆነ ለማየት አያዳግትም።     
     

No comments:

Post a Comment