Friday, June 13, 2014

የመቐለ ንግደ ቤቶች እና ስያሜዎቻው ‘’ ዲያና ቡና ቤት ‘’ ‘’Diyana coffe house ‘’ ይህን የንግድ ቤት ስም ያየሁት አምና መቐለ እንደመጣን ሃገሩን ለማየት ስዞር ነበር ። ቡና የሀገራችን ባህላዊ መጠጥ ሲሆን ከሌሎች ሀገራት ካለው የሚለየው በአፈላል ስርአቱ ነው ዲያና ቡና ቤትም በባህላችን መሰረት ቡና እይተፈላ የሚሸጥበት ቤት ነገር ግን ስያሜው የእንግሊዟ ልዕልት ነው ። ከታሪክ አንጻር እንኳን ብናይ ልዕልት ዲያና የኢትዮጵያ ቡና የሚተቀዋወቁ እንኳን አይመስለኝም ። ይሄ ትንሽ ምሳሌ ነው ። አብዛኞቹ ንግድ ቤቶች መጠሪያቸወ የምዕራብያውያን ነው ለምን ? ንግድ ቤቶቹን ተወት እናድርግ እና እስቲ እራሳችንን እንመልከት ( የመቐለ ዩኒቨርስቲ ተማሪዎች ) ። በወሬያችን መሃል እንግሊዘኛ ጣል ካለደረግን የምንሞት የሚመስለን እንግሊዘኛ አቀላጥፎ የሚናገር ሰውን እንደ ምሁር ስለምናይ የእንግሊዘኛ ትምህርትን ስንማር እንድ ቋንቋች ሳይሆን እንደ ዕውቀት መለኪያ የምናይ ትርጉሙን እንኳን በውሉ የማናውቀውን የእንግሊዘኛ ዘፈን አፍቃሪያን የሆነው ለምንድን ነው ? ምክንያቱም እንግሊዘኛ መናገር ፦ - ኣራዳ - ጎበዝ - ዘመናዊ ሙድ ያለው ( ትክክለኛው የአማርኛ ፍቺው ምንድነው ?) ሙድ ያለን የሆንን ስለሚመስለን ነው ። እንዲሁም አብዛኞቻችን የሃይስኩል ተማሪዎች እያለን እንግሊዘኛ እንማራለን እናጠናለን ነገርግን ኣማርኛ ዞር ብለን አናየውም ( ከተወሰኑ ተማሪዎች በስተቀር ) ። መንግስትም እራሱ በ 12ኛ ብሄራዊ ፈተና ወቅት አማርኛ ሳይኖር እንግሊዘኛ ይፈትናል አማርኛ ያልተፈተነው ስላወቅነው አይደለም እንግሊዘኛ ግን እንደትልቅ ነገር ትምህርት ባለበት ሁሉ ስንማር እንገኛለን ። የኔ ጥያቄ ለምን እንግሊዘኛ ተማርን አይደለም ለምን እንግሊዘኛ ከቋንቋነት በዘለለ መልኩ ትኩረት ተሰጠው ? ነው የኔ ጥያቄ ። በፊት በፊት የቤተሰቦቻችን ስም ስንጠራ ለምሳሌ እናታችንን ፦ እማዬ ፣ እማ ፣ እቴቴ ፣ እታባ ወ.ዘ.ተ አሁን ግን mami , mom , ma ,mother e.t.c እንደዚ እያልን መጥራት ከጀመርን ሰነባብተናል ። ስለዚህ እኛ የዪኒቨርሲቲ ተማሪዎች ደግሞ የነዚህ የንግድ ቤቶች ቀንደኛ ተጠቃሚ ነን እነዚን ንግድ ቤቶች የሚያስተዳድሩት ሰዎች አብዛኞቹ እንደእኛ ወጣቶች ናቸው ስለዚህ እንሱም እንደእኛ የሰለጠኑ መስሏቸው በእውቀት የመጠቁ ፣ አራዳ ፣ አሪፍ የሆኑ ስለሚመስላቸው ቤቶቹን በባዕድ ሀገር ስም ይሰይሟቸዋል ። በገበያ ደረጃ የሰሩት ስራ በደንብ እደግፋለው ምክንያቱም ስያሜዎቻቸው ከደንበኞቻቸው ፍላጎት የመጡ ናቸው ብዬ አስባለው ። ደንበኛህ የምዕራብያውያን አድናቂ ከሆነ የሱን ፍላጎት ማሟላት ግድ ይላል ። በዚረገድ ንግድ ቤቶች ትክክለኛ የገቢያ( Marketing ) ስራ ሰርተዋል ብዬ አምናለው ። እንደ ሀገር እና እንደ ባህል ትርጉም የሌለው ፣ ባዳነት የሚጎላበት ከ እውቀት የጸዳ ስያሜ ነው ። ‘’ዲያና’’ ስንቶቻችን ነን የምናውቃት ? ለኛስ ምን አድርጋለች ? እነዚህን ጥያቄዎች የሚመልስ የለም ። ሳባ ፣ ጣይቱ ፣ ዘውዲቱ ወ.ዘ.ተ.. እነዚህ ግን ታሪኮቻችን ናቸው ። እነሱን ለንግድ ቤቶች ስያሜ ብናደርጋቸው ስማቸው እንዳይጠፋ ታሪካቸው እንዳይረሳ ይረዳን ነበር ። መጪው ትውልድ ሳባን ታውቃታለህ ሲባል’’ ማነች ? ዘፋኝ ነእ ኦ … አክትረስ ‘’ የሚል አይመስላችሁም ? በመጨረሻም ይህ የባህል ወረራ ከቀጠለ ወደ ማንመለስበት አዘቅጥ ውስጥ ሊያስገባን ይችላል ፤ ለቀጣዩም ትውልድ የምናወርሰው ቋንቋ እንኳን ለማግኘት እንቸገራለን እላለው ። ስለዚህ የሁላችንም ርብ ርብ የሚጠይቅ ስራ በመሰራት የግድ ይለዋል መልዕክቴ ነው ።



                የመቐለ ንግደ ቤቶች እና ስያሜዎቻው  
     ‘’ ዲያና ቡና ቤት ‘’ ‘’Diana coffee house ‘’ ይህን የንግድ ቤት ስም ያየሁት አምና መቐለ እንደመጣን ሃገሩን ለማየት ስዞር ነበር ። ቡና የሀገራችን  ባህላዊ መጠጥ ሲሆን ከሌሎች ሀገራት ካለው የሚለየው በአፈላል ስርአቱ ነው ዲያና ቡና ቤትም በባህላችን መሰረት ቡና እይተፈላ የሚሸጥበት ቤት ነገር ግን ስያሜው የእንግሊዟ ልዕልት ነው ። ከታሪክ አንጻር እንኳን ብናይ ልዕልት ዲያና የኢትዮጵያ ቡና የሚተቀዋወቁ እንኳን አይመስለኝም ። ይሄ ትንሽ ምሳሌ ነው ። አብዛኞቹ ንግድ ቤቶች መጠሪያቸወ የምዕራብያውያን ነው;;
                                    ለምን ?

       ንግድ ቤቶቹን ተወት እናድርግ እና እስቲ እራሳችንን እንመልከት ( የመቐለ ዩኒቨርስቲ ተማሪዎች ) ። በወሬያችን መሃል እንግሊዘኛ ጣል ካለደረግን የምንሞት የሚመስለን እንግሊዘኛ አቀላጥፎ የሚናገር ሰውን እንደ ምሁር ስለምናይ የእንግሊዘኛ ትምህርትን ስንማር እንድ ቋንቋች ሳይሆን እንደ ዕውቀት መለኪያ የምናይ ትርጉሙን እንኳን በውሉ የማናውቀውን የእንግሊዘኛ ዘፈን አፍቃሪያን የሆነው ለምንድን ነው ?                                                         
                             ምክንያቱም እንግሊዘኛ መናገር                          
                                                               - ኣራዳ
                                                               - ጎበዝ
                                                               - ዘመናዊ
       ሙድ ያለው ( ትክክለኛው የአማርኛ ፍቺው ምንድነው ?) ሙድ ያለን የሆንን ስለሚመስለን ነው ። እንዲሁም አብዛኞቻችን የሃይስኩል ተማሪዎች እያለን እንግሊዘኛ እንማራለን እናጠናለን ነገርግን ኣማርኛ ዞር ብለን አናየውም  ( ከተወሰኑ ተማሪዎች በስተቀር ) ። መንግስትም እራሱ በ 12ኛ ብሄራዊ ፈተና ወቅት አማርኛ ሳይኖር እንግሊዘኛ ይፈትናል አማርኛ ያልተፈተነው ስላወቅነው አይደለም እንግሊዘኛ ግን እንደትልቅ ነገር ትምህርት ባለበት ሁሉ ስንማር እንገኛለን ። የኔ ጥያቄ ለምን እንግሊዘኛ ተማርን አይደለም ለምን እንግሊዘኛ ከቋንቋነት በዘለለ መልኩ ትኩረት ተሰጠው ? ነው የኔ ጥያቄ ።

በፊት በፊት የቤተሰቦቻችን ስም ስንጠራ ለምሳሌ እናታችንን ፦ እማዬ ፣ እማ ፣ እቴቴ ፣ እታባ  ወ.ዘ.ተ   አሁን ግን  mami , mom , ma ,mother   e.t.c   እንደዚ እያልን መጥራት ከጀመርን ሰነባብተናል ።

      ስለዚህ እኛ የዪኒቨርሲቲ ተማሪዎች ደግሞ የነዚህ የንግድ ቤቶች ቀንደኛ ተጠቃሚ ነን እነዚን ንግድ ቤቶች የሚያስተዳድሩት ሰዎች አብዛኞቹ እንደእኛ ወጣቶች ናቸው ስለዚህ እንሱም እንደእኛ የሰለጠኑ መስሏቸው በእውቀት የመጠቁ ፣ አራዳ ፣ አሪፍ የሆኑ ስለሚመስላቸው ቤቶቹን በባዕድ ሀገር ስም ይሰይሟቸዋል ።

      በገበያ ደረጃ የሰሩት ስራ በደንብ እደግፋለው ምክንያቱም ስያሜዎቻቸው ከደንበኞቻቸው ፍላጎት የመጡ ናቸው ብዬ አስባለው ።  ደንበኛህ የምዕራብያውያን አድናቂ ከሆነ የሱን ፍላጎት ማሟላት ግድ ይላል ። በዚረገድ ንግድ ቤቶች ትክክለኛ የገቢያ( Marketing ) ስራ ሰርተዋል ብዬ አምናለው ። 

      እንደ ሀገር እና እንደ ባህል ትርጉም የሌለው ፣ ባዳነት የሚጎላበት ከ እውቀት የጸዳ ስያሜ ነው ። ‘’ዲያና’’ ስንቶቻችን ነን የምናውቃት ? ለኛስ ምን አድርጋለች ? እነዚህን ጥያቄዎች የሚመልስ የለም ።

     ሳባ ፣ ጣይቱ ፣ ዘውዲቱ ወ.ዘ.ተ..  እነዚህ ግን ታሪኮቻችን ናቸው ። እነሱን ለንግድ ቤቶች ስያሜ ብናደርጋቸው ስማቸው እንዳይጠፋ ታሪካቸው እንዳይረሳ ይረዳን ነበር ። መጪው ትውልድ ሳባን ታውቃታለህ ሲባል’’ ማነች ? ዘፋኝ ነእ ኦ … አክትረስ ‘’ የሚል አይመስላችሁም ? 

     በመጨረሻም ይህ የባህል ወረራ ከቀጠለ ወደ ማንመለስበት አዘቅጥ ውስጥ ሊያስገባን ይችላል ፤ ለቀጣዩም ትውልድ የምናወርሰው ቋንቋ እንኳን ለማግኘት እንቸገራለን እላለው ። ስለዚህ የሁላችንም ርብ ርብ የሚጠይቅ ስራ በመሰራት የግድ ይለዋል መልዕክቴ ነው ።

No comments:

Post a Comment