Friday, June 13, 2014

ጥሩ እቃ ጥሩ ማስታወቂያ



ጥሩ እቃ ጥሩ ማስታወቂያ
     ሃገራችን በሁሉም ነገር ወደ ሗላ ቀርታለች። በስልጣኔ፣ በእድገት፣በቶክኖሎጂወዘተ ወደ ሗላ ቀርታለች። በማስታወያም ቢሆን ከሌሎች ሃገራት አንጻር በጣም ወደሗላ የቀረች ነች። ለዚህም ምሳሌ ሊሆን የሚችው የሃገራችን ባለሃብቶች እንዱሁም ትልልቅ ድርጅቶች ማስታወቂያ ድርጅታቸውን ለማስተዋወቅ የሚሰራ ሳይሆን እስተዋዋቂውን ለመርዳት ተብሎ የሚሰራ አድርገው ይቆጥሩታል። በነሱ አስተሳሰብ ማስታወቂያ ገንዘብ እንደማባከኛሰ አድርገው ይቆጥሩታል ለአዚህም ምክንያታቸው ጥሩ ምርት ካመረትኩ ምርቴ ጥራት ካለው ማስታወቂያ አያስፈልገኝም ብለው ያምናሉ
 በመጀመሪያ ማስታወቂያ ምንድን ነው ለምንስ ይጠቅማል?
    ማስታወቂያ ማለት የአንድን ድርጅት ምርትይም አገልግሎት ለህብረተሰቡ የሚያስተዋውበት የያሳይበት መንገድ ነው አላማውም፤
       አዲስ ምርት ከሆነ ሰው እንዲያውቀው
       በጥቂቱ የሚታወቅ ከሆነ የንን ለማስፋፋት
        በደንብ የሚታወቅ ከሆነ ባለው ለመቀጠል ደንበኞቹንም የምርቱ ታማኝ ተጠቃሚ እንዲሆኑ ለማድረግ ነው።
        ምንም ያህል አንድን ምርት በጥራቱ እነደኛ ቢሆንም ነገር ግን ከሱ በጥራት የሚያንሱ ነገር ግን ማስታወቂያ የሚያሰሩ ድርጅቶች በገበያም ሆነ በመታወቅ ይበልጡታል።
        ማስታወቂያ ማለት አንድን ድርጅት ከ ማህበረሰቡ ጋር የሚያገናኝ ድልድይ ማለት ነው። ታዲያ ይህ ድልድይ ከሌለ ምን ሊፈጠር እንደሚችል ለማሰብ አይከብድም። ስለዚህ ይህ ድልድይ ከሌለ ሰው ወደ ድርጅቱ ለመሄድ ይቸገራል። ኮካኮላ በአለማችን ላይ ካሉ ምርጥ ምርጥ የለስላሳ መጠጦች ውስጥ አንደኛው ነው። ሆኖም ግን ከአመት አመት እነዳስተዋወቀ ነው። ኮካ ኮላ ማስታወቂያ የሚሰራው ጥሩ ምርት ስላልሆነ አይደለም።
         በኢኮኖሚክስ Boom or Peak የሚባል ነገርአለ ይህም ማለት እድገት የመጨረሻው ደረጃ ላይ ሲሆን ማለት ነው። ኮካኮላም በጥራቱም ሆነ በመታወቅ በጣም ትልቅ ደረጃላይ ያለ ድርጅት ነው። ታዲያ ይህንን ያህል ዕውቅና ያለው ለምን ማስታወቂያ ያሰራል ገንዘብስ እያባከነ አይድልም ወይ? የሚሉ ሰዎች አሉ ነገር ግን ማስታወቂያ የሚሰራው ያሉት ደንበኞች ታማኝ ደንበኛ  እንዲሆኑ እና ከዚህ በሗላ የኮካ እጣፈንታ እድገት ሳይሆን ውድቀት ስለሚሆን ባለበት እንዲቀጥል ማስታወያው ስለሚያግዘው ነው።
       አብዛኞቹ በሃገራችን ውስጥ የሚመረቱ ምርቶች በጥራታቸው ከሌሎች ሃገራት ምርቶች ይልቃሉ። ለምሳሌ ጫማ፣ እና የቆዳ ምርቶች አንዳንዶቹ ናቸው። ማህበረሰቡ ግን የሚጠቀመው የሃገሩን ምርት ሳይሆን የቻይና ሴንቴቲክ የሆኑ ውድ ጫማዎችን። በጥራቱ ምርጥ ሆኖ ሳለ ማስታወቂያ ባለመስራቱ እና ባለመታወቁ ገበያ ያጣል እንዲሁም ለኪሳራ ይጋለጣል ምክንያቱም ጥራቱን ጠንካራነቱን ስላልተናገረ።
         ከዚህም በተጨማሪ የግንባታ ባለሙያዎች ለደህንነታቸው ሲሉ በስራ ወቅት የሚጠቀሙት የደህንነት ጫማ አላቸው። ይህ ጫማ የሚሰራው ከ ቆዳ እና ውስጡ ከአደጋ የሚከላከል ብረት አለው። ይህንን ጫማ በሃገራችን ውስጭ በጥራት ይሰራል ነገር ግን ብዙ የግንባታ ባለሙያዎች የሚገዙት የሌሎች ሃገራትን ምርት ነው። ነገር ግን እነሱ የሚጠቀሙት ጫማዎች በሃገራችን ከሚመረቱ ምርቶች
                                             1 በጥራት ያንሳል
                                             2ከንጹህ ቆዳ አይሰራም
                                             3 መጥፎ ጠረን ያመጣል
                                             4 ውስጥ ያለው ብረት እግርን ያሳምማል እና ጠካራ አይደለም  
ሆኖ ም ግን ሰዎች ብዙዉን ጊዜ የሚጠቀሙት ይህንን ከሃገራቸው ምርት በጥራት የሚያንሰውን ምርት ነው። ታዲያ ይህንን የሚያደርጉት ለምን ይበስላችሗል? በጥራቱ የሚበልጠው የሀገራችን ምርት ነው ነገር ግን በተጠቃሚዎች ዘንድ ስለማይታወቅ ሰዎች ይህንን ምርት ሊጠቀሙ አትችሉም። ስለዚህ የሃገራችን ባለሃብቶች ማድረግ ያለባቸው ጥሩ ምርትይ እያመረቱ ጥሩ ማስታወቂያ መስራት ነው። ለጥሩ ምርት የሚያስፈልገው ጥሩ ማስታወቂያ ነውና።   

No comments:

Post a Comment